ለስምንት አመታት የአልጋ ቁራኛ የሆኑት አባት የምለው አለኝ ይላሉ


“ካቅሜ በልጦ ልጆቼን የማጎርሰዉ አጥቼ እጄን ዘርግቻለሁ”

አባት የተራቡ ልጆቹን አይን እያየ ሳግ ባነቀዉ ልሳን ይሄን ሲናገር መስማት ምነኛ ልብ ይሰበራል...
ታያል ባወቀ ብርቱ አናፂ ነበር፡፡ ከራሱ አልፎ የሚወዳት ሚስት እና የሚራራላቸዉን ልጆቹን አልብሶ እና አብልቶ ያሳድር ነበር፡፡ በስራዉ ላይ ሳለ ያልታሰበ ህመም ደረሰበት፡፡ አቅሙን ሳያጣዉ፤ ጤና ከዳዉ፡፡ አለሁ ባይ ደራሽ በሌለበት ለስምንት አመታት የአልጋ ቁራኛ ሆነ፡፡
ድንገት በወደቀብኝ “የመገጣጠምያ ህመም” ተይዤ ልጆቼ አይኔ ስር ተራቡብኝ አለን፡፡ ዉድ ኢትዮጲያዉያን እንዲህ ካለዉ ያልታሰበ መከራ ፈጣሪ ይሰዉራችሁ፡፡ ብርቱዉ አናፂ ህመምተኛ ጎኑን የሚያሳርፍበት መጠለያ እንኳ የለዉም፡፡ ጅምር ህንፃ ዉስጥ ዘበኞች አስጠግተዉት ከነ ልጆቹ ያድራል፡፡ ዉድ የሀገሬ ልጆች ቀና ልባችሁ ቢፈቅድ ታያል በሀገር ዉስጥ መታከም ይችላል፡፡ በጎ ፍቃዳችሁ ቢራራ ልጆቹ የሚቀምሱትን ያገኛሉ፡፡ ስለ ልጆቹ በህይወት መኖር ስንል ልባችንን ለመልካም እንፍቀድና ካለን ላይ ጥቂት እናካፍላቸዉ፡፡
በምስኪን ልጆቹ ህይወት ላይ አንዲት የተስፋ ቀን እንጨምርባት፡፡ በታያል የልብ ስብራት ላይ ብርሀን እንፈንጥቅ፡፡
“መልካምነት ከፈጣሪ የሚመክሩበት የፅድቅ መስመር ነዉ፤ ስለ ፈጣሪ ስንል መልካም እናድርግ፡፡”
  • Anonymous

    1,000ብር
  • Anonymous

    1,395ብር
No results have been found

Nuro Bezede Media

Created Jun 02, 2020 Addis Ababa

Featured Campaign

2,395ብር of 50,000ብር goal

4.79% Raised by 2 Donations ህክምና