የእናራ የሠላም አንድነትና ልማት ፎረም የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ


የእናራ የሠላም አንድነትና ልማት ፎረም እንቅስቃሴን ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ/ፕሮግራም/ Fund rising to Enara peace, unity and development forum የገቢ ማሰባሰቡ ዓላማ እናራ የሠላም፣ አንድነትና ልማት ፎረም/አገር በቀል ሲቪክ ማህበር/ ለሚያደርጋቸው የሠላም እሴት ግንባታ በተከታታይነት ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ለሚሰጣቸው የአቅም ማሳደጊያ አጫጭር ስልጠና እና ውይይት ጠቅላላ ወጪ የሚውል፤ ሕዝብ ለሕዝብ ግኑኝነትን ለማሻሻል በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ለተሞክሮ ልውውጥና ለጋራ ግኑኝነት ማጎልበት ተግባር ወጪ የሚውል፤ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ያለውን ትውልድ ለመፍጠር የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝ ለወጣቱ የሀገሩንና ሕዝቡን ታሪክ፣ ጠቃሚ ባህልና እሴቶች አንፃር ይበልጥ ግንዛቤ ለማሳደግ የንባብ ባህልን በዚያው ለማሳደግ ፎረሙ ለሚያደርገው የንባብ ዘመቻ ለመፅሐፍት ግዢና ስርጭት የሚውል፤ ፎረሙ የሕዝቡ ባህላዊ ግጭት አፈታት አደረጃጀቶችና የህብረተሰብ የልማት አደረጃጀቶች ለሠላሙ የተሻለ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አደረጃጀታቸውንና አሰራራቸውን ለማሻሻል የሚውል ገንዘብ ይሆናል፡፡ የገቢ አሰባሰቡ የሚውልባቸው ዝርዝር ተግባራትና የገንዘቡ መጠን ተራ ቁጥር የተግባሩ ዓይነት መለኪያ መጠን ጠቅላላ የገንዘቡ መጠን ምርመራ ብር ሣንቲም 1 በሠላም እሴት ግንባታ የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠና ቁጥር 400 120¸000 00 ለ4ቱም አካባቦዎች 2 የሕዝብ ለሕዝብ ግኑኝነት ቁጥር 200 50¸000 00 በ4ቱም 3 ለንባብ ዘመቻ ቁጥር 2000 225¸000 00 ለመፅሐፍት ግዢ 4 አገር በቀል አደረጃጀት አቅም ለማጎልበት ቁጥር 25 375¸000 00 አደረጃጀቶቹ 5 የወጣቶችንና ሴቶችን የልማት ተሳትፎ ለማጎልበት ቁጥር 550 137¸500 00 በአባላት ቁጥር 6 ለጠቅላላ ሥራ ማስከጃ ቁጥር 25 55¸000 00 7 ጠቅላላ ድምር በብር 962¸500 00 ስለ ፎረሙ እናራ የሠላም፣ አንድነትና ልማት ፎረም/ሀገር በቀል ሲቪክ ማህበር/ በአገሪቱ ይበልጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተስተዋሉ የመጡትን ግጭቶችና አለመረጋጋቶች መነሻ በማድረግ በዋነኛነትም ለሠላም እሴት ግንባታና ፀጥታው መስፈን፣ በሕዝብ ለሕዝብ መልካም ግኑኝነትና አብሮነት መሻሻል፣ እርስ በርስ በመረዳዳትና በበጎ አድራጎት ተግባር ቢሎም አገር በቀል የሕብረተሰቡ የግጭት አፈታት ባሕልና ሥርዓት መጎልበትን ታሳቢ በማድረግ በሐምሌ 2010 ዓ.ም አጋማሽ እንቅስቃሴ ጀምሮ በነሐሴ 29/12/2010ዓ.ም ይፋዊ ምስረታውን በማድረግ ከፌዴራል ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በአገር በቀል ድርጅት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት በቀን 19/09/2011ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 4172 የተመዘገበበት ሕጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት በሸኚ ደብዳቤ ቁጥር 36/Acso/4292 በቀን 23/09/20011ዓ.ም በማግኘት እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅር/ማህበር/ ነው፡፡ የፎረሙ የእንቅስቃሴ ዋነኛ ዒላማ ፎረሙ በመርህ ዕቅዱ፣ በሕገ ደንቡ/መተዳደሪያ ደንቡ/፣ በፕሮጀክቶቹና በሌሎች ሰነዶቹ ያስቀመጣቸው ዋነኛ ዓላማና ተግባራቱ በሠላም እሴት ግንባታ፤ የሕዝብ ለሕዝብ ግኑኝነት ጎልብቶ አብሮነትና አንድነት እንዲሻሻል፤ ለሠላም እሴት መጎልበት አጋዢ የሆኑ አገር በቀል የህብረተሰቡ አደረጃጀቶች እንዲጎለብቱ፤ የህብረተሰቡን የእርስ በርስ መረዳዳት ባሕል ለማጎልበት፤ የወጣቱንና ሴቶችን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ፤ ወጣቱ ትውልድ የቀደምት አገሩንና ሕዝቦቹን ታሪክ እንዲረዳና የሕዝቦቹን ጠቃሚ ባሕልንና እሴቶቹን ለመንከባከብ በሚደረገው ጥረት ብሎም የመንግሥትና የህብረተሰቡን ርብርቦሽ አጋዥ በመሆን የድርሻውን ማበርከት ይሆናል፡፡ የእሠአል ፎረም የእንቅስቃሴ አድማስ ፎረሙ በሕገ-ደንቡ፣ በመርህ ዕቅዱ፣¸በፕሮጀክቶቹና በሌሎች ዶክመንቶቹ በማመላከት ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያገኘባቸው የእንቅስቃሴ አካባቢዎችም
  1. በደ/ብ/ሕ/ ክ/መ/ የም ልዩ ወረዳ፣
  2. በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን በሠኮሩ ወረዳ እና በጅማ ከተማ
  3. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ናቸው፡፡
የፎረሙ የግኑኝነት መረጃ፡-
  • የፎረሙ የሂሳብ አካውንት - 1000267711268
  • FB ሚዲያ- እናራ ሚዲያ
  • ፌስ ቡክ/fb/- እናራ ሰላም
  • የፎረሙ ኢሜል- enaraforum @gmail.com
  • በፌዴራል የፎረሙ የምዝገባ ቁጥር- 4172 mobil- 0911702087/0944702604/0936190409
There are no donations
No results have been found

enara peace unity and Dev.t forum

Created Oct 10, 2020 የም ልዩ ወረዳ፣ ጂማ ዞን እና በአ.አ በንፋስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ወረዳ 6

0ብር of 962,500ብር goal

0.00% Raised by 0 Donations በጎ አድራጎት