About us
-
About Degafi Fund
Degafi.com is operated and managed by BTnet Technology Solutions plc in Ethiopia and Degafi, Inc. in the United States of America. it is professional crowed funding platform supported by FDRE Civil Society Agency in Ethiopia. Degafi Fund is originally called Eneredada.com which was founded on Jan 17, 2018 as a funding platform operating manually with select Charity Organizations. After the Corona Virus changed the way of live Eneredada has since changed its name and rebranded it's platform to accomodate other sectors that need help. WE are now officially called Degafi Fund under degafi.com.
Btnet Technology solution is engaged in importing and making softwares to solve problems.We provide Local and International Clients IT consulting services and custom software development with professionals located Locally and internationally.
----
News Coverage!
እንደጎ ፈንድ ሚ ኢትዮጵያዊ የድጋፍ ገንዘብ ማሰባሰቢያ የኮምፒውተር ሥርዓት መተግበሪያ ተዘጋጀ
ደጋፊ ዶት ኮም የተሰኘ እንደጎ ፈንድ ሚ ለተለያዩ ዓላማዎች የማህበረሰብ ዕርዳታ ማሰባሰቢያ የኮምፒውተር ሥርዓት (ሲሰተም) መተግበሪያ ተዘጋጀ።
አቶ ቢኒያም ነገሱ የቢቲ ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅና የመተግበሪያው አዘጋጅ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ ዓላማዎች በጎ ፈንድ ሚ የዕርዳታ ገንዘብ ማሰባሰብ እየተለመደ መምጣቱን አስታውሰው ይህ አሰራር ያሉትን ክፍተቶች በማየት ለኢትዮጵያውያን በሚስማማ መልክ አዲስ መተግበሪያ በኩባንያቸው በኩል ተዘጋጅቶ ወደሥራ እየገባ ነው።
“ደጋፊ ዶት ኮም” ለበጎ አድራጎት፣ ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለሀይማኖትና መሰል ጉዳዮች ከህብረተሰቡ ድጋፍ ለማሰባሰብ ያሰቡ ተቋማት ወይንም ግለሰቦች ተመዝግበው እና የአገሪቷን ሕጎች የድርጅቱን መስፈርት ባልተቃረነ መልኩ ወደገንዘብ ማሰባሰብ ሥርዓት እንደሚገቡ አቶ ቢኒያም አስረድተዋል።
ረጅ ግለሰቦችና ተቋማት ቃል የሚገቡትን ገንዘብ ሲስተሙ በሚያዛቸው መሰረት በሄሎ ካሽ፣ አሞሌ ፣ ሲቢኢ ብር፣ ኤም ብር፣ በባንክ ሲያስገቡ እንደሚመዘገብና በመጨረሻም ገንዘብ አሰባሳቢዎቹ ገንዘቡን ላቀዱት ዓላማ ብቻ እንደሚያውሉት የግዴታ ውል እንደሚገቡ አቶ ቢኒያም ተናግረዋል።
ገንዘቡን የሚሰበስበው አካል ወይም ተቋም በቀላሉ በሲስተሙ አማካኝነት የማበረታቻ ሽልማቶችን ያለገደብ ማዘጋጀት ይችላሉ። በተጨማሪም ረጅ አካላት በሚቀመጠው መስፈርት መሰረት ሲረዱ የማበረታቻ ሽልማት እንደሚያገኙ የተናገሩት አቶ ቢኒያም ይህ ከጎ ፈንድ ሚ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።
በውጭ አገር የሚኖሩ የዲያስፖራ አባላት ገንዘብ መርዳት ሲፈልጉ በሲስተሙ አማካይነት ተገቢውን ሒደት አልፈው ገንዘቡን በስዊፍት በባንክ ገቢ በማድረግ መደገፍ እንደሚችሉ፣ በቀጣይ ሲስተሙን ለዲያስፖራው ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ደጋፊ ዶት ኮም በቅርቡ ተመርቆ ወደሥራ እንደሚገባም አቶ ቢኒያም ነገሱ አረጋግጠዋል።