Requirement
-
ለሁሉም ዘመቻ ፈጣሪዎች አጠቃላይ መመሪያዎች
-
የዘመቻ ፈጣሪዎች ከቅጂ መብት ባለቤቱ ፈቃድ ሳያገኙ የቅጂ መብት የተያዘባቸው ቁሳቁሶችን ወይም ማንኛውንም ፎቶግራፍ ፣ የንግድ ምልክቶች ወይም አርማ ያለ መብትን የሚጻረር ማንኛውንም ነገር እንዲጠቀሙ አልተፈቀደላቸውም ፡፡ ማንኛውንም ይዘት የቅጂ መብት የሚጥስ ሆኖ ከተገኘ እንደዚህ ዓይነት ይዘቶች ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ይወገዳሉ። ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ በማንኛውም መንገድ ህገ-ወጥ ሆነው ያገ ኘናቸውን እነዚያ ዘመቻዎች ካጣራን እና አውነት ሆነው ከተገኙ ይወገዳሉ እና ዘመቻውን የፈጠረውም አካል በሕግጋታችን መሠረት በሕግ ፊት ይዳኛል፡፡
-
የዘመቻ ፈጣሪዎች በDegafi ፈንድ ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲዎች መቀበል እና መስማማት የሚኖርባቸው ሲሆን በየወቅቱ በDegafi ፈንድ አስፈላጊነታቸው ታምኖበት የሚቀየሩ የቅርብ ጊዜ የፖሊሲ ለውጦችንም መከተል እና መቀበል አለባቸው፡፡ ይህንንም Degafi ፈንድ በድህረ ገጹ ላይ በየጊዜው ለተጠቃሚዎች የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
-
የዘመቻ ፈጣሪዎች ለእያንዳንዱ የዘመቻ ምድብ እና ዓይነት የሚያስፈልጉት መስፈርቶችን እና ሰነዶች ሁሉ ሟሟላት አለባቸው ፡፡ ዘመቻው ከመጽደቁ በፊትም አስፈላዚ ማስረጃዎች ና ዶክመንቶች ወደ mereja@degafi.com መላክ አለባቸው፡፡
-
ከሥነ-ምግባር ወይም ከማህበራዊ እሴቶች ጋር የማይጣጣም ማንኛውንም የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ የመዝጋት ወይም ያለመቀበል መብቱ የተጠበቀ ነው።
-
ከተጠቀሱት እና በግልጽ ከተገለፁት ምድቦች በስተቀር ለጊዜው ከየትኛውም አካል የዘመቻ ፈጠራ ጥያቄዎችን መቀበል አይችልም ፡፡ ነገር ግን DegafiFund ለሌላ ሲቪል-ያልሆኑ ማህበራት ድርጅት በአሳማኝ ምክያቶችቸ ገንዘብ ማሰባሰብ ይችላል፡፡ ይህም ሌሎች ምድብ በሚለው ስር የሚካተት ይሆናል።
-
ሁሉም የዘመቻ ፈጣሪዎች ዘመቻዎ እንዲደረስበት ከተፈለገ ደረጃ እዲደርስ እና ማህበረሰቡ አንዲያውቀው ለማድረግ በ ማህበራዊ ሚዲያ አገናኞች (ፌስቡክ ፣ ቴሌግራም ወይም ትዊተር ፣ እና ሌሎችም መንገዶች ) በመጠቀም በተከታዩቻቸው እና በሌሎች የአላማው ደጋፊች አማካኝነት በማሰራጨት ዘመቻቸውን የማስተዋወቅ ሃላፊነት አለባቸው ፡፡ ይህም ዓላማዎቹን ለማሳካት ለምናደርገው ጥረት ከፍተኛ ድጋፍ ይኖረዋል፡፡
-
ሁሉም የዘመቻ ፈጣሪዎች ማንኛውንም ዘመቻ ለመፍጠር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ መመስረት እና በቌሚነት በኢትዮጵያ መኖር አለባቸው ፡፡
-
ሁሉም የዘመቻ ፈጣሪዎች በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እና ሌሎች የህግ አካላት ሁሉንም አስፈላጊ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ፡፡
-